Aug. 20, 2017

ግዕዝ እንደ ብሄራዊ ፊደል የመጠቀም አዋጭነት !

የሺሃሳብ አበራ /በአማራ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋዜጠኛ/

"አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት" የሚል ጥናታዊ ፁሁፍ አብርሃም ቀጀላ በተባሉ ተመራማሪ ቀርቧል፡፡ በጥናቱ፣ በ16 ኛው መቶ ክፍለዘመን በአፍሪካ መካ መዲናዋ ሀረር በግዕዝ የተፃፈ ቁራዓን እንደነበር ተተንትኗል፡፡ የኦሮመኛ መፅሀፍ ቅዱስ፣ በ1884 ዓም በአናሲሞስ ነሲብ( በአባ ገመቹስ) አማካኝነት ተተርጉሟል፡፡አናሲሞስ፣ በኦሮመኛ ቋንቋ በወለጋ እንዲሰብኩ አፄ ምኒሊክ ድጋፍ እንዳደረጉላቸውም ተብራርቷል ፡፡

ግዕዝን በመጠቀም የኦሮመኛ ቋንቋ ከ 1884-1983 ዓም ለ 100 ዓመት ያህል ቆይቷል፡፡ ይህ በይፋ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ስብከት የተጀመረበት እንጂ ቁራዓንም በ 16 ኛው ክፍለዘመን ከአረበኛ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ እንደነበር ፃህፊው አብርሃም ቀጀላ አስፍረዋል፡፡

ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በአቻነት የምትጠራው ሳ ጋዜጣም የግዕዝ ፊደልን በመጠቀም ትታተም ነበር፡፡ አባ አናሲሞስ ነሲብ እና አስቴር ጋኖ የኦሮመኛ መዝገብ ቃላትን በግዕዝ አሳትመው ነበር፡፡ ነገር ግን ግዕዝ በኦሮመኛ ቋንቋ የረጅም ዘመን ታሪክ ቢኖረውም ፣የኦሮሞ ልሂቃን ግዕዝን የሰሜኑ ቋንቋ በማድረግ ቅርቡን ሸሽተው የሩቀን የላቲን ፊደል አምጥተዋል፡፡ ይህም በስራዓተ ፅህፈቱ አዋጭ እንዳልሆነ የኮምፒውተር የግዕዝ ቴክኖሎጂስቱ የሰንዳፋው ተወላጅ ዶክተር አበራ ሞላ ይመክራሉ፡፡

ምሳሌም ያስቀምጣሉ፣ሁሉም የእንግሊዘኛ ፊደላትን የያዘው ይህ አርፍተ ነገር ነው THE QUICK BROWN FOX JUMPS OVER THE LAZY DOG. ይህ አርፍተ ነገር በላቲን 36 ቀለማትን ሲይዝ፣በቁቤ( በኦሮ) 45 ቀለማትን ይይዛል፡፡ በግዕዝ ሲሆን ግን ወደ 24 ይወርዳል፡፡
ዶክተር አበራ ሞላ፣ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የግዕዝ ፊደልን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ፈጠራ ከ ዛሬ 30 ዓመት ጀምረው ይዘው ቀርበዋል ፡፡እያሻሽሉትም ነው፡፡ ግዕዝን ከኮምፒውተር ጋር በማስተዋወቅ ከአሜሪካ መንግስት በ 2007 አዲስ የፈጠራ መብትም አግኝተውበታል፡፡ምናልባትም ጤፍ የዱቄት፣የጤና አዳም መድሀኒትነት በስዊዘርላንድ እንደተመዘገበው የግዕዝ ፊደላትም በጀርመኖች ና በካናዳዎች ሊመዘገብ ይችል ነበር፡፡
ነገር ግን ለ 40 ዓመታት ያህል ባደረጉት ጥረት ግዕዝን በኢትዮጵያዊያን እንዲመዘገብ አድርገዋል፡፡ ከአፍሪካ ብቸኛው ፊደል የሆነው ግዕዝ በዋሽንግተን ዮኒቨርስቲ የግዕዝ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፊሰር ሀምዛ፣ከአረበኛ ፣ከግሪከኛ(ከፅርዕ)፣ እብራይስጥና ላቲን ቋንቋዎች ጋር የሚተካከል የታሪክ ሀብት አለው፡፡

በዋሽንግተን፣በቶሮንቶ እና በጀርመን ዮኒቨርስቲዎች ትምህርቱ ይሰጣል፡፡ በተለይም ከዶክተር አበራ ሞላ ፊደሉን ከቴክኖሎጂ ጋር ካስተዋወቁት በኃላ ዓለም አቀፋዊ ጥንታዊ ቋንቋነቱ እየገፋ መጥቷል፡፡ 75% የግዕዝ ፊደላትን የሚጠቀመው አማርኛም በአሜሪካ ቬርጂኒያ ግዛት የትምህርት
ቋንቋ እንደሆነ አቶ አብርሃም ቀጀላ በጥናታቸው ገልፀዋል፡፡ አማርኛ የተለያዮ የአሜሪካ ግዛቶችን ጨምሮ በእስራኤልም የስራ ቋንቋነት እየታጨ ነው፡፡ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ራሱ የፈጠረውን እና ከሀገሩ ቋንቋ ከግዕዝ የተቀበለውን ልዮ ፊደል መጠቀሙ አግዞታል፡፡
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት የሚያገለግለው ግዕዝ ብሄር ዘለል እና ሳይንሳዊ ቋንቋ ነው፡፡አንዳንዶች የሀይማኖት ቋንቋ አድርገው ይስሉታል፡፡ ግን ብቻ አይደለም፡፡
አቶ አብርሃም ቀጀላ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ ከ 13 -15 ሚሊየን የክልሉ ነዋሪዎች ኦሮመኛ አይችሉም፡፡ ፊደሉን የግዕዝ ሆኖ ቢሆን ግን በተሻለ ሁኔታ መቀራረብ ይፈጠር ነበር፡፡አቶ አብርሃም በፁሁፋቸው ኦሮመኛ የግዕዝ ፊደልን ተጠቅም የሀገሪቱ ሁለተኛ የስራ ቋንቋ ቢሆን፣ የተሻለ ብሄራዊ መግባባትናቅርብ ይፈጠር ነበር ይላሉ፡፡

ዶክተር አበራ ሞላም በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ፡፡ በአማርኛ የስነፁሁፍ ታሪክ ውስጥ እንደነፀጋየ ገብረመድህን፣ አለቃ ተክለ እየሱስ ዋቅጅራ፣ በዓሉ ግርማ፣ይልማ ደሬሳ ወዘተ ስመጥር ፃህፍት ለግዕዝ የተሻለ ቅርበት የነበራቸውና ኦሮመኛንበግዕዝ የሚጠቀሙ ነበሩ፡፡፡
ግዕዝ እስከ 1832 ዓም የቤተክርስቲያን ዋነኛ መስበኪያ ቋንቋነበር፡፡ከ 1832 በኃላ፣ የግዕዝ መፅሐፍ ቅዱስ በአባ ዮሀንስ አማካኝነት ከ 10 ዓመት ጥናት በኃላ ሙሉ በሙሉ ወደ አማርኛ ተመልሷል፡፡በግዕዝ የስነፁሁፍ ታሪክ ውስጥ በ 14 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ የሸዋ ነገስታት ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ እንደ መፅሀፈ ነገስት ከአረበኛ ወደ ግዕዝ ተመልሰዋል፡፡ ታምረ ማርያም ተደርሶበታል፡፡ 80 በላይ ቋንቋዎች ያሏት ኢትዮጲያ በአሁኑ ወቅት የስራቋንቋ እንጂ ብሄራዊ ቋንቋ የላትም፡፡ ግዕዝን ሁሉም ቋንቋዎች በመፃፊያነት ቢገለገሉበት ፣ፊደሉ በቂ ነው፡፡በሀገር ውስጥ የቋንቋ አፀግብሮቱም ስለሚስፋፋ የተሻለ መቀራረብን ሊፈጥር እንደሚችል ዶክተር አበራ ሞላ እና አቶ አብርሃም ቀጀላ በጥናታቸው አረጋግጠዋል ፡፡

ሮፊሰር ፍቅሬ ቶሎሳም አፋን ኦሮም ግዕዝን ቢጠቀም የተሻለ እንደሚሆን አብራርተው ፅፈዋል፡፡

http://ethiopiazare.com/…/4414-oromiffa-with-geez-by-abreha…

በሌላ በኩል ደግሞ የግዕዝን ቋንቋ ጥንታዊነት እና የኢትዮጵያ ቀደምትነት በመዘንጋት እንዲህ አይነት ሙግቶችም እየተነሱ ነው፡፡

" ኩሽ እጆቿን ወደ እግዜአብሄር ትዘረጋለች እንጂ ኢትዮጲያ የሚልየመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል በግሪከኛ እና በእብራይስጥ የለም፡፡ 45 ጊዜ ስሟ ይጠራል የሚለው በኩሽነት ነው”

-ፓስተር በንቲ ኡጀሉከጀርመን

 https://www.opride.com/
ሱዳን እጆቿን ወደ እግዜአብሄር ትዘረጋለች እንጂ ኢትዮጲያ በመፅሀፍ ቅዱስ አትታወቅም- የሱዳን የታሪክ ተመራማሪዎች
2009GC
፡፡ እኛ የምንደራደረው የኢትዮጵያ ስም ኩሽ ከሆነ ነው- አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ሚያዚያ 20 ቀን 2009 ዓም፡፡
ከግዕዝ ሴማዊነት ርቆ ለመሸሽ የሚደረግ የህልም ሩጫ ይመስላል፡፡ ግዕዝ የኢትዮጵያን የቤተክርስቲያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የ2 ሺ ዓመት ታሪክ ጠቅሎ የያዘ ቋንቋ ነው፡፡ ግዕዝን ካለመቀበል አልፎ የኢትዮጵያ ስያሜ ላይም ጥያቄ እየተነሳ ነው፡፡

አሻም ሚዲያ/Asham Media